Log in

I forgot my password

Who is online?
In total there are 4 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 4 Guests

None

[ View the whole list ]


Most users ever online was 64 on Tue May 06, 2014 11:26 am
New Sites
አዲስ ሳይት

ኢትዮ ሲንግልስ
Meet Ethiopians Singles | Register Now

ኢትዮ ፎረም
Ethiopians Forum
Latest topics
» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Thu Oct 23, 2014 5:12 pm by nenash

» Sxs Film Hindi
Tue Oct 21, 2014 9:31 pm by nenash

» Kingdom Age Hack Tool V2.5
Tue Oct 21, 2014 8:00 am by nenash

» Ore Wa Kanojo O Shinjiteru! 02 | Checked
Mon Oct 20, 2014 3:57 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Sun Oct 19, 2014 2:20 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Sun Oct 19, 2014 2:17 pm by nenash

» Hide My Ip Activation Key 5.4
Sun Oct 19, 2014 11:14 am by nenash

» Windows 8 All Editions Activator.exe
Sat Oct 18, 2014 10:01 pm by nenash

» ?????? Anime Anime03 ?? ?? ?? ???? ?? Blu-ray?
Sat Oct 18, 2014 8:08 pm by nenash

» Rhcsa Rhce Red Hat Linux Certification Practice Exams With V
Sat Oct 18, 2014 6:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Sat Oct 18, 2014 12:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Sat Oct 18, 2014 12:05 pm by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Thu Oct 16, 2014 1:20 am by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Thu Oct 16, 2014 1:16 am by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:31 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:24 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Wed Oct 15, 2014 9:23 pm by nenash

» [Most_popular]_tudung_bj_abg_opis_3gp-adds
Wed Oct 15, 2014 1:06 pm by nenash


የስብሀት ወጎች

Go down

የስብሀት ወጎች

Post by yaredlove on Sat Oct 03, 2009 8:17 am

ጠይና ይስጥልኝ :: ይህቺ ቤት የጋሽ ስብሀት ገ /እግዚአብሄር የዝክር ቤት ናት :: ሌሎች ስለ ጋሽ ስብሀት ያሉትንና እሱም ከጻፋቸው ውስጥ እጄ የገባውን አለፍ አለፍ እያልኩ አካፍላችኌለሁ ቤት ያፈራውን አብረን እንቀማመስ በማለት ነው :: እናንተም አዋጡ :: ለዛሬ ዘነበ ወላ ካዘጋጀለት የህይወቱ አልበም ውስጥ በመጀመሪያው ገጽ ላይ ያለችዋንና በራሱ የእጅ ጽሁፍ ካሰፈራት አስተያየት ልጀምር ::

በልጅነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቶ ተነስቼ ሲያሳዩኝ "" ይሄን ነው የምመስለው ?"" ብዬ ገረመኝ :: ፎቶውን ግን አምኘዋለሁ :: ሌሎችን አንስቶ አይቸዋለሁዋ ! ለካ ከውጭ ሲያዩኝ ይሄን ነው የምመስለው :: ሌላ ቀን ደሞ ድምጼን በቴፕ ሰማሁና አሁንም ገረመኝ :: ስናገር እኔ የምሰማው ሌላ የቴፑ ድምጽ ሌላ ! ዘመናት አለፉ (ቀን መቁጠሪያው ግን አመታት አለፉ ይላል ) እኔም ሆንኩ ዘነበ ይህን የምታነቡትን መጽሀፍ ገና በሀሳባችን ሳይመጣ እሱ ስለ ህይወትና ስነ -ጽሁፍ እንዳወራለት ሁኔታዎችን አመቻቸ :: ስናወራ ....ስናወራ ...ስናወራ ...ሳናስበው ይሄ መጽሀፍ ብቅ ማለት ጀመረ :: እኔ ተናገርኩ እሱ መዘገበ ጻፈ :: በስድሳ አመት እድሜዬ ይህ ዘነበ በሚከተሉት ምእራፎች እንደምታነቡት በቃላት ፎቶ አንስቶኝ አየሁ :: ለካ በደግ አይን ሲያዩኝ ይህን እመስላለሁ :: ገርሞኝም አላባራ !!
avatar
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 25
Location : Ethiopia/Nazareth

View user profile http://www.yared.tk

Back to top Go down

እነሆ ቀዳሚና ተከታይ

Post by yaredlove on Sun Oct 04, 2009 12:07 am

እነሆ ቀዳሚና ተከታይ የሀላፊውና የመጪው ትውልድ አባል ሆነን ተገናኘን :: ጋሼ የአዲሱ ትውልድ አባል ከቶውንም እማይባልለት መዕራፍ ላይ ደርሷል :: የአላፊው ትውልድ አባል ለመሆን በመጨረሻዋ የህይወት ጠርዝ ላይ ይገኛል :: የእኔም ትውልድ ይከተለዋል :: ህይወት ዕልፍ አዕላፍን ያሸጋገርችው በቅብብሎሽ ነው :: እንደ ወንዝ በምትሀትዋ በውስጣችን ለዘመናት ፈሳለች :: ወደፊትም እንደዚሁ ሂደቱ ይቀጣላል ::
ከዕለታት አንድ ቀን "" ዘነበ ""

"" አቤት ጋሼ ?""

"" ሞትን እንቅደመው ?""

"" እሺ ግን እንዴት ?""

"" ከማውቀው የማስታውሰውን ሁሉ ልንገርህ !""

"" ማለፊያ ""

"" የሚጣፈውንም የማይጣፈውንም ነው የምነግርህ ""

"" እየያዝኩ ነው ""

"" እንቀጥል ሔንድርክ ቫን ሉን ( Hendrik Van Loon) የሚባል የደች ዘር አሜሪካዊ ደራሲ The Wandering Jew የሚባል ልብ -ወለድ ጽፏል :: ባጭሩ ላጫውትህ :: በእኛ ቌንቌ ስትተረጉመው " ከርታታው ይሁዲ " ልትላት ትችላለህ :: ይሁዲው ሲፈርድበት ሊፈታተነው ከማይችለው ቀና ብሎ ሊያየው ከማይገባ ሰው ጋር ለዘላለሙ ተቀያየመ :: "" ድንጋይ ቢወድቅብህ ይጎዳሀል ብትወድቅበትም ይጎዳሀል " እንዲሉ አልኩት ::

" እ ! ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጌተ -ሰማኒ ጉብታ ሊሰቅሉት መስቀል አሸክመው እየገረፉ ይወስዱታል :: እየተንገዳገደ እየወደቀ እየተነሳ ያዘግማል :: በአካሉ ውስጥ የቀረችው እንጥፍጣፊ ጉልበት ነች :: በዚህ መሀል በዛ ባልታደለ ይሁዲ ደጅ ያልፋል :: የቤቱ ጥላ አጥልታለች :: ጌታ ኢየሱስ እዛ ጋ ትንሽ እፎይ ለማለት ጔጉቶ እየተንገዳገደና እየተወላገደ ጠጋ ሲል ይሁዲው አየውና "" ምን እዚህ ትሽመደመድብናለህ ፈጠን ብለህ ሂድ ! ቀርፋፋ ! "" አለው :: ኢየሱስም ቀና ብሎ አየውና " እኔስ እየሄድኩ ነው አንተ ግን እስከምመለስ እዚሁ ትቆየኛለህ " አለው :: " ያ ከርታታ ይሁዲ አሁንም ባለማችን ላይ በህይወት አለ :: በልዩ ልዩ ሀገር እይተዘዋወረ ይኖራል :: አይሞትም :: ኢየሱስ ወደ አለማችን ዳግም እስኪመጣ ይጠብቀዋል :: የዛን ጊዜም እድለኛ ከሆነ ነው የሞትን ጽዋ የሚጠጣት :: እስከዚያ ድረስ ግን መንከራተቱን ይቀጥላል :: ባለበት ሀገር :: ለረጅም ጊዜ አብረውት የኖሩት ሰዎች ተገርመው " አንተ አታረጅም አትሞትም እንዴ ?' ሲሉት " በቃ አውቀውኛል ማለት ነው ' ይልና ሀገር ቀይሮ የእርግማን ኑሮውን ይቀጥላል :: አንተ ራስህ የአረብ መልክ ያለው ሰው ካጋጠመህ ተጠራጠር :: ምናልባት ከርታታው ይሁዲ ሊሆን ይችላል :: እኔ እንኴን አንድ ቀን ተረት ሰፈር አይቼዋለሁ " አለና ጋሼ ከልቤ አሳቀኝ ::
avatar
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 25
Location : Ethiopia/Nazareth

View user profile http://www.yared.tk

Back to top Go down

Back to top


 
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum